×

SOMI 's video:

@በረመዳን የኸይር ስራ ጥሪ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው በአሜሪካ, አውሮፓ እና በሁሉም የዓለም ሃገራት ለምትገኙ ወንድም እህቶቻችን በሙሉ እንኳን ለታላቁ የተከበረው የረመዳን ወር በሰላም አደረሳችሁ:: በአሜሪካ የሚገኘው ሰላም ፋውንዴሽን እነሆ ታላቅ የምስራች ይዞልን መጥቷል:: ለመጀመሪያ ጊዜ ታላቁ መስጂድ እውን ሊሆን ነው ፡፡ ከትልቁ የነጩ ቤተመንግስት በራፍ ላይ ፣ የኛው የሀበሻ ሙእሚን ወንድሞቻችን በአላህ ርዳታ ያሳኩት የአሌግዛንድሪያው የሃበሾቹ ሰላም ፋውንዴሽን ኢስላማዊ ማዕከልና መስጂድ፡፡ በመልካም ስነምግባር የታነጸ፣ የሰዎችን አስተሳሰብ እና እምነቶች የሚያከብር እንዲሁም አላህን ፈሪና ምድርን አሳማሪ የሆነ ወርቃማ ትውልድ እንዲፈጠር ከፍተኛ የሆነ ትግል አማራጭ የሌለው መፍትሄ የሆነው ለዚህ ነው፡፡ ይህንን የእምነት ነጻነት በመጠቀም የአላህን እና የነቢዩን አደራ መወጣት የሁሉም ሙስሊሞች ግዴታም የሆነው ለዚህ ነው፡፡ ለዚህም ሲባል በርካታ የሙስሊም ኮሚኒቲዎች በዚህ ጊዜ ወርቅ ሳይሆን የሚቀልጥ በረዶ በሆነበት ዓለም ጊዜያቸውን ለአላህ በመሰዋት ከሃላፊነቶቻቸው ጎን ለጎን ይህንን የደዕዋ ኃላፊነት በከፍተኛ ወኔ ሲወጡ ይስተዋላል፡፡ ከነዚህ መካከል ሰላም ፋውንዴሽን አንዱ ነው፡፡ ሰላም ፋውንዴሽን ከተመሰረተ _ ዓመታትን ያስቆጠረ በሃገረ አሜሪካ የሚገኝ እና እናት ሃገር ኢትዮጲያን ጨምሮ በአሜሪካ በርካታ የበጎ አድራጎትና የዳዕዋ ስራዎችን ሲሰራ እና የሚሰሩትንም ሲያግዝ የቆየ ተቋም ነው፡፡ እነሆ አሁንም በዋሺንግተን ዲሲ አካባቢ አሌግዛንድሪያ ፣ ቨርጂኒያ ውስጥ 1.3 ሚሊዮን ዶላር በማውጣት ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጲያዊያን እጅ የሚገኝ 87,000 ስኩዌር ፊት ወይም 8000 ካሬ የሚሆን ስፋት ያለው የመስጂድ እና ኢስላማዊ ማዕከልን ለመገንባት የሚያስችል ስፍራ በመግዛት በኪራይ እና ከቦታ ጥበት ምክንያት ምናልባትም ለኛ ለኢትዮጲያዊያን እንግዳ የሆነውን የጁሟዓን ሶላት በ 4 የተለያዩ ተከታታይ ሰዓቶች ለመስገድ ያስገደዳቸውን ሁኔታ በቃህ ለማለት በቅተዋል፡፡ ምስጋና ለአላህ የተገባ ይሁን፡፡ ሰላም ፋውንዴሽን ይህንን መስጂድ እውን ለማድረግ በርካታ በአሜሪካ እና በተቀሩት የዓለም ክፍሎች የሚገኙ ወንድም እህቶቹን በዚህ ታሪካዊ መስጂድ ላይ አሻራቸውን እንዲያሳርፉ የድረሱልኝ ጥሪ ያቀርባል፡፡ እናም ከፊታችን ማርች 15 እስከ 17 ድረስ በወርሃ ረመዳን ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር በቀጥታ ስርጭት ያካሄዳል፡፡ This stream is created with

221

4
SOMI
Subscribers
280K
Total Post
461
Total Views
1.2M
Avg. Views
11.3K
View Profile
This video was published on 2024-03-16 17:58:10 GMT by @SOMI on Youtube. SOMI has total 280K subscribers on Youtube and has a total of 461 video.This video has received 221 Likes which are lower than the average likes that SOMI gets . @SOMI receives an average views of 11.3K per video on Youtube.This video has received 4 comments which are lower than the average comments that SOMI gets . Overall the views for this video was lower than the average for the profile.SOMI #PRISMLiveStudio has been used frequently in this Post.

Other post by @SOMI